ኢተምድ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ፡፡

ኢተምድ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ፡፡

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት 9‚299 የአገልግሎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የምርት ጥራት የላብራቶር ፍተሻ፣ የወጪና ገቢ ምርት ኢንስፔክሽን እና የሰርተፍኬሽን አገልግሎቶችን በመስጠት ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲኖር እና ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት እንዲሰፍን ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡እነዚህም አገልግሎቶች ለ6‚853 የምርት ናሙናዎች የላብራቶር ፍተሻ አገልግሎት፣ ለ2‚110 ገቢ እና ወጪ የምርት ናሙናዎች እና 10 መርከብ የስንዴና የአፈር ማዳበሪያ ጭነት የኢንስፔክሽን አገልግሎት እና ለ326 የሰርተፍኬሽን አገልግሎቶች ይገኙበታል፡፡