
- 20 Mar 2023
- Menbere Abreham
- Blog
- Comments: 0
በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት/ኢተምድ/ በመገኘት የሥራ ጉብኝት አደረጉ።
የጉብኝቱ አላማም በድርጅቱ የሚሠጡት የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች እና በዓለም ባንክ ፕሮጀክት እየተሰሩ ያሉትን የአቅም ግንባታ ሥራዎች በአካል በመገኘት ያሉበትን ደረጃ መጎብኘት እና በቀጣይ ድርጅቱ የሚሰጠውን አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ እንዲያከናውን ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ተቋም እንዲሆን ያለመ ነበር፡፡
Related Posts
የኢተምድ የሥራ አመራሮችና ሰራተኞች በሰበታ ሀዋስ ወረዳ ሁለተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አከናወኑ፡፡
የኢተምድ የሥራ አመራሮችና ሰራተኞች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ፡፡
ኢተምድ በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ፡፡