ኬሚካል እና የማዕድን ፍተሻ

የኢተምድ ኬሚካልና የማእድን ፍተሻ ላብራቶር ከ90 በላይ ለሚሆኑ ማእድናት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካሎች እናየመሳሰሉ ምርቶች ከ460 በላይ የፍተሻ ባህሪያት ላይ የጥራት ፍተሻ ያከናውናል፡፡ እነዚህ ምርቶች በመመዘኛ መስፈርቶች ላይ በተገለጸው መሰረት ለተመረቱበት ዓላማ ስለመዋላቸው (ውጤታማነት)፣ ስለደህንነታቸው እና ከሚፈለገው የጥራት ደረጃ ተገዢነት አንፃር ይፈተሻሉ፡፡

በኢተምድ የኬሚካል እና የማዕድን ፍተሻ ላቦራቶር ከሚፈተሹ ምርቶች በጥቂቱ

  • ሲሚንቶ ፣
  • የመዋቢያ ምርቶች፣
  • ቀለም፣
  • ለፅዳት አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካሎች ፣
  • ሃይድሮጂን ፐርኦክሳይድ ፣
  • ቆዳ
  • ብረት ፣
  • የአካባቢ ናሙናዎች ( አፈር፣
  • ሳኒታይዘር
  • ለኢንዱስትሪ እና ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካሎችና የመሳሰሉት………
በእነዚህ ምርቶች ላይ የሚፈተሹ ዋና ዋና የፍተሻ ባህሪያት
1.መርዛማ/ጎጂ ማዕድናት/ Heavy Metals
2.የምርት ይዘት/ Composition
3.የምርት ግብዓት አይነት/Ingredients
4.የንፅፅር ፍተሻ/ Comparison test