ግብርና እና የእርሻ ግብዓት ፍተሻ

የኢተምድ የግብርና እና የእርሻ ግብዓቶች ፍተሻ ላብራቶር ከ150 በላይ የተለያዩ የግብርና ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች፣ የእንስሳት መኖ እና ለማዳበሪያነት አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካሎችና የመሳሰሉ ምርቶች ከ1‚500 በላይ የፍተሻ ባህሪያቶች ላይ የጥራት ፍተሻ ያከናውናል፡፡ እነዚህ ምርቶች በመመዘኛ መስፈርቶች ላይ በተገለጸው መሰረት ለተመረቱበት ዓላማ ስለመዋላቸው(ውጤታማነት)፣ ስለደህንነታቸው እና ከሚፈለገው የጥራት ደረጃ ተገዢነት አንፃር ይመዘናሉ፡፡

 በኢተምድ የግብርና እና የእርሻ ግብዓቶች ፍተሻ ላቦራቶር ከሚፈተሹ ምርቶች በጥቂቱ

  • ማር፣
  • ቅቤ፣
  • በርበሬ፣
  • ሰም፣
  • እርጎ፣
  • የታሸገ ፈሳሽ ወተት፣
  • ጥቁር ሻይ፣
  • የሻይ ቅጠል፣
  • ኮረሪማ፣
  • ነጭ ስኳር፣
  • ጥሬ ስኳር፣
  • ጠንካራ ውህድ ማዳበሪያ እና የመሳሰሉት                                                                                                                                                       በእነዚህ ምርቶች ላይ የሚፈተሹ ዋና ዋና የፍተሻ ባህሪያት
    
    1.መርዛማ/ጎጂ ማዕድናት/Heavy Metals
    
    2.የምርት ይዘት/Composition )
    
    3.የምርት ግብዓት አይነት/Ingredients
    
    4.የፀረ-ተባይ ቅሪት/ pesticide residue )
    
    5.የፈንገስ ዝርያዎች/ Mycotoxin
    
    6.የስኳር ዓይነቶች /Sugar profile