ኢንስፔክሽን

ኢንስፔክሽን፡ የምርት ንድፍን ፣ምርትን ፣አገልግሎትን  የስራ ሂደትን ወይም የሥራ ቦታን  ከተቀመጠለት  መስፈርት/ መመሪያ ወይም ከሙያዊ ምዘና አንፃር መዝኖና ገምግሞ ተስማሚነትን የማረጋገጥ ሂደት ነው፡፡

ኢተምድ ገለልተኛ የሦስተኛ ወገን እና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የኢንስፔክሽን አገልግሎትን በISO/IEC 17020 መሰረት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ምርቶች ይሰጣል፡፡

  • ለቅባት፣ ጥራጥሬ እና ለሰብል ምርቶች (በኢንስፔክሽን)
  • ለሕፃናት አልሚ ምግቦች (በናሙና አወሳሰድ)
  • ለቆርቆሮ  ምርት (በናሙና አወሳሰድ)

ከላይ ከተዘረዘሩት የኢንስፔክሽን አገልግሎቶች በተጨማሪ ኢተምድ ገለልተኛ የሦስተኛ ወገን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የኢንስፔክሽን አገልግሎትን በ(ISO/IEC 17020)  መሰረት  በየደረጃው ባሉ የምርቶች  ሂደቶች (ከማምረት ጀምሮ እስከማጓጓዝ) ላይ አገልግሎቶች ይሰጣል፡፡

   √√ የፋብሪካ ግምገማ
        የማምረቻ ፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪዎች/  ተገቢውን የማምረት ስርዓት ተከትለው በማምረት ሂደት ላይ  መሆናቸውን ማረጋገጥ

   √√ የቅድመ ምርት ኢንስፔክሽን  
      ለፋብሪካ በጥሬ ዕቃነት የሚያገለግሉ የግብርናም ሆነ ሌሎች ግብዓቶች/ጥሬዕቃዎች/  ተገቢውን የጥራት ባህሪያቶች  ማሟላታቸውን ማረጋገጥ

√√ በማምረት  ወቅት ኢንስፔክሽን 
         በፋብሪካ/በኢንዱስትሪዎች/  ለሚመረቱ ምርቶች በማምረት ሂደት ወቅት የሚፈለገውን  የጥራት ባህሪያት ሳያሟሉ የሚመረቱ ምርቶች የመለየትና ተፈላጊው             የጥራት  ባህሪያት አሟልተው እንዲመረቱ ማስተካከል

 √√ የቅድመ ጭነት ኢንስፔክሽን
        የማምረት ሂደቱ ተጠናቆ ምርቱ በመታሸግ ለጭነት ዝግጁ በሚሆንበት ወቅት ከመጨረሻው ምርት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ  በታወቀው ስታስቲካል ናሙና              መረጣ   ቴክኒክ መሰረት ናሙና ተመርጦ የምርቱን መጠን፣ብዛት፣አገልግሎት፣ከለር፣ቅርፅ፣የማሸጊያ ዝርዝሮችንና መመዘኛዎች ተሟልተው መገኘታቸውን                    ለማረጋገጥ  የሚከናወን የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዘርፍ ነው
          √√በጭነት ላይ  ክ ትትል

      የቅድመ ጭነት ኢንስፔክሽን  መጠናቀቅን ተከትሎ ምርቱ በሚጫንበት ወቅት የመጓጓዝ ሁኔታውን ምቹነት ንፅህና የመጫኛ እቃዎቹን ጥንካሬና ምርቱን     ከመድረሻው ለማድረስ   ብቁ መሆናቸውን ኢንስፔክት ማድረግ ነው፡፡