የሚመገቡት ምግብ ጥራቱን የጠበቀ እንደሆነ ያምናሉ?
በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ኢንዱስትሪው ከጥራት መጓደል ጋር በተያያዘ ከመቼውም ጊዜ በባሰ ተግዳሮት አጋጥሞታል። በውጤቱም ሸማቹ በሚገበየው የምግብ ውጤቶች ላይ እምነት እንዳይኖረው ምክንያት ሆኗል። ታዲያ ለምንመገበው ምግብ ምን ዋስትና ይኖረናል?
የምግብ ጥራትን ማገረጋገጥ የዘወትር ተግባራችን ቢሆንም ስንቶቻችን ጥራቱ በፍተሻ ላብራቶር ስርዓት ተፈትሾ ያለፈን ምግብ እንጠቀማለን? ይህም ማለት የምግቡ ይዘትና በማሸጊያው ላይ ያለው መግለጫ የተገናዘበ መሆኑን የሚገልጸውን የጥራት ምልክት በማየት እንገዛለን? በ1980ቹ በስፔን ሀገር በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለምግብነት በሚውል የተበከለ ዘይት ለማብሰያነት በመጠቀማቸው የሞቱ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ደግሞ በቻይና የህጻናት ወተት መያዥያ የፕላስቲክ ጠርሙስ ለጤና ጎጂ በሆነ ኬሚካል በመበከሉ የተጠቃሚ ሕጻናቱን ጤና አደጋ ውስጥ አስገብቶ እንደነበር የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የተከለሰው የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001፡2015 quality management system) ለቴክኖሎጂ ለውጥ፣ ለተለያዩ የንግድ ዘርፎችና ለዓለም አቀፍ ንግድ የሚኖረው ምላሽና በቀላሉ ጥቅም ላይ እንዲውል ሆኖ ተዘጋጅቷል
ከተጠቃሚዎች ስለ አሰራር ስርዓቱ የተሰጡ ግብረመልሶች አዎንታዊ ናቸው። በእንግሊዝ ቻርተርድ የጥራት ኢንስቲቲዩት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሲሞን ፌሪ የአሰራር ስርዓቱን በተቋም መጠቀም “ማርሽ ቀያሪ ነው” በማለት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እማኝ ምስክሮችን በመጥቀስ ስርዓቱን በተቋማቸው መትከላቸው አዎንታዊ ለውጥ ማየት እንዳስቻላቸው ይገልጻሉ። የቦይንጉ ዓለም አቀፍ ኤሮስኮፕ ቡድን መሪ አለን ዳኔልስ በበኩላቸው በደረጃው ክለሳ ላይ የተሳተፉ ሲሆን የአሰራር ሥርአቱን መጠቀም ተጨባጭ ለውጥን በተቋም የሚያመጣና ተቋሙን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው፤ ተቋማት በሥራዎቻቸው ስኬትን ለማየት ከፈለጉ ደረጃውን መጠቀም የግድ ይላቸዋል በማለት ይናገራሉ። ለዚህ ነው የተከለሰው የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 9001፡2015 quality management system) ለሁሉም ተቋማት እንደ መልካም ዜና የሚቆጠረው። ይህ በዘመናዊ መንገድ የተከለሰ ደረጃ ወቅቱን ያገናዘቡ ፍሬ ነገሮችን ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መልኩ አካቶ ቀርቧል። የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ድርጅቶች እንደሚመሰክሩት የአሰራር ስርዓቱ ለተቋማቸው ተጨባጭ ለውጥ እንዳመጣ እና ይሄው ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማስቻል ስራዎቻቸው ጥራት እንዲኖራቸው አስችሏል።
ስለ ተስማሚነት ምዘና የፍተሻ ላቦራቶር ውጤቶች ሊታወቁ የሚገቡ ነጥቦች
በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ በገዢና ሻጭ መካከል መተማመንን መገንባት እጅግ አስቸጋሪና የአንድ ጀምበር ስራ ባይሆንም ሶስተኛ ወገን የፍተሻ ላብራቶር አገልግሎትን ለመጠቀም ትክክለኛና አስተማማኝ ውጤት የሚሰጥ የፍተሻ ላብራቶር ማግኘት ቁልፍ ሚናን ይጫወታል።
ስለሆነም አምራቾች፣ ላኪዎችና አስመጪዎች እንዲሁም አገልግሎት ሰጪና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቻቸውን ከማስፈተሻቸው በፊት ሊጠይቁት የሚገባቸው መሰረታዊ ጥያቄ ቢኖር የፍተሻ ላብራቶር አገልግሎት ሰጪው አካል ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለውን የላብራቶር ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO/IEC 17025 laboratory management system) ይከተላል ወይ የሚል ይሆናል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት በንግዱ መድረክ መተማመንን ለመፍጠር የሦስተኛ ወገን የጥራት ማረጋገጫን መያዝ ወሳኝ በመሆኑና ISO/IEC 17025ን መተግበር ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትና ቀጣይነት ያለው የፍተሻ ውጤት እንዲኖር የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የደንበኛን ፍላጎት ለማርካትና በውጤቱ እንዲተማመን ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። የተስማሚነት ምዘና ተቋማት የፍተሻ ላቦራቶር የሚከተሉት መሰረታዊ ባህርያት ሊኖራቸው ይገባል:-